አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር በመፈራረሟ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የደስታ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ኦርዲን÷ ሥምምነቱ ለኢኮኖሚያዊ፣ ለማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ዕድገት ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ሥምምነቱ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ነው ያመላከቱት፡፡