Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

 ሥምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር ነው- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር የባሕር በር ለማግኘት የተፈራረመችው ሥምምነት የሀገራቱን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ሰነድ ከሶማሌ ላንድ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርማለች።

አቶ ኡሞድ ስምምነቱን ተከትሎ÷ለመላው የጋምቤላና የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን እውን የሚያደርግ ስምምነት መፈራረሟ በዲፕሎማሲው ረገድ ትልቅ ስኬት እንደተገኘ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት እምነታቸውን መሆኑንም ተናግረዋል።

ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት እና ለአፍሪካ ቀንድ ትሥሥር የላቀ ፋይዳ እንዳለውም አንስተዋል።

Exit mobile version