Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው አሉ አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ እየተከተለች ያለችው ፖሊሲ የተለያዩ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ሥምምነት ሰነድ ከሶማሌ ላንድ ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርማለች።

ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ ስምምነቱን ተከትሎ÷ ለመላው የአፋር እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

በመልዕክታቸው÷ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ እየተከተለች ያለው ፖሊሲ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው ሲሉ አውስተዋል፡፡

ስምምነቱ የኢትዮጵያን የባሕር በር የማግኘት ፍላጎት እውን የሚያደርግ፣ የባሕር በር አማራጮችን የሚያሰፋ፣ የሁለቱን ወገኖች የፖለቲካ፣የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ አዲስ የትብብር ምዕራፍ የሚከፍት፣ የቀጠናው ሀገራት በጋራ የማደግና በጋራ የመበልፀግ ራዕያቸውን ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ በመሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

Exit mobile version