አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕላዊ የውሀ ማቀዝቀዣ የሆነው የዕደ-ጥበብ ውጤት “አልብሪክ” በዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክት (ብራንድ) ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማግኘቱን የቤኒሻንጉል ክልል የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ምስኪያ አብደላ አስታወቁ፡፡
ይህንንም ተከትሎ ኃላፊዋ ለክልሉ ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የቤኒሻንጉል ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመሆን÷ “አልብሪክ”ን በዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክት ሆኖ እንዲመዘገብ መሥራታቸው ተገልጿል፡፡
ሥራውን ተከትሎም ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የንግድ ምልክት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማግኘት መቻሉን ነው ኃላፊዋ ያስረዱት፡፡
የዕደ-ጥበብ ምርቶችን በንግድ ምልክትነት (ብራንድ) ማስመዝገብ መቻሉ ኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ለማስጠበቅ እንደሚጠቅምም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በዓለም አቀፍ ደረጃ የገበያ ትስስርን በመፍጠር ተሳታፊ ለመሆን ያስችላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!