አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ነገ በሐረር ከተማ በሚጀመረው ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ መድረክ ላይ ለመታደም ወደ ሥፍራው አቅንተዋል፡፡
ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ምክር ቤቶች አፈ ጉባዔዎች እና ከፍተኛ አመራሮችም በመድረኩ እንደሚታደሙ ተገልጿል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ዛሬ ድሬዳዋ ከተማ ሲገቡ÷ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሐረሪ ጉባዔ አፈ ጉባዔ አቶ መህየዲን አሕመድ፣ የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፈቲያ አደን እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል መባሉን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!