Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በወቅታዊ የክልሉ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በሆሳዕና ከተማ እየመከረ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሳውን ጨምሮ በክልሉ የሚገኙ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችና የፖሊስ ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል፡፡

ምክክሩ በዋናነት በክልሉ አጠቃላይ የፀጥታ አሁናዊ ሁኔታ፣ ባጋጠሙ ችግሮችና በተወሰዱ መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ አዳዲስ የፀጥታ ስጋቶች ካሉ መለየት እና መፍትሄ ማስቀመጥ ላይ እንደሚያተኩር የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል ወቅቱ የገና በዓል የሚከበርበት በመሆኑ ጸጥታ ለማስከበር እየተሰሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።

Exit mobile version