Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በአዲስ አበባ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየምን ጨምሮ ተገንብተው አገልግሎት እየሠጡ ያሉ ትላላቅ ፕሮጀክቶችንና ሰውተኮር ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝታቸው በኋላም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ አስተዳደሩ የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለል እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የበርካቶችን ሕይወት እየቀየሩ መሆናቸውን ተገንዝበናል ብለዋል፡፡

የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ኪሎ ሜትር ሙዝየምን ጨምሮ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉ ትላላቅ ፕሮጀክቶች የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር ለትውልድ የሚተላለፉ ስራዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው÷ አስተዳደሩ የነዋሪውን ሕይወት በዘላቂነት ለመቀየር፣ ከተማዋን ለኑሮና ለስራ ምቹ ለማድረግ እየሠራ ነው ማለታቸውን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የመዲናዋን ገፅታ የሚቀይሩ በርካታ እቅዶችን ከነዋሪው ጋር እየተመካከርን እየተገበርን ነውም ብለዋል ከንቲባዋ ብለዋል፡፡

Exit mobile version