Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኦሮሚያ ክልል ከ3 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ተጠገነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ 3 ሺህ 96 ኪሎ ሜትር መንገድ መጠገኑን የኦሮሚያ መንገዶችና ሎጂስቲክስ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ለጥገና ሥራውም 393 ሚሊየን 741 ሺህ 522 ብር ወጭ መደረጉን ነው የቢሮው ምክትል እና የመንገድ አሥተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ታመነ ታደሠ (ኢ/ር) የተናገሩት፡፡

የመንገድ ጥገና ሥራውም የመደበኛ እና ድንገተኛ ጥገናን ያካተተ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በ2016 የበጀት ዓመትም 7 ሺህ 18 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመጠገን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዓመቱን የጥገና ሥራ ለማከናወንም 1 ቢሊየን 152 ሚሊየን 638 ሺህ 458 ብር መመደቡን ጠቅሰዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

Exit mobile version