Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ የአዲስ አበበ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው የተመረቀው፡፡

በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ድጋፍ የተከናወነው የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የምድረ ግቢ የማስዋብ ሥራ፣ የስፖርት ሜዳዎች ግንባታ፣ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ ሙከራ እንዲሁም የአጥር ሥራን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የትምህርት ቤቱ ማስፋፊያ ሥራ በ”ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ መርሐ ግብር የተከናወነ መሆኑን የከንቲባ ጽ/ህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version