Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪና ሌሎች አመራሮች በክልሉ በከተማና በገጠር እየተከናወኑ የሚገኙ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ከፕሮጀክቶቹ መካከልም የአስፋልት መንገድና የኢኮ ፓርክና መዝናኛ ፕሮጀክት እንዲሁም የማምረቻና የመሸጫ ሼዶችን ተመልክተዋል፡፡

እንዲሁም የንጹሕ መጠጥ እና የመስኖ ግንባታ ፕሮጀክቶችን፣ አዳዲስ የገጠር ጠጠር መንገድ ግንባታ፣ ጥገናና ሌሎችንም ፕሮጀክቶች ጎብኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ÷ በክልሉ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ በጥራት፣ በፍጥነትና በሃላፊነት መስራት ይገባልም ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የተገነቡ የማምረቻና መሸጫ ሼዶችን በአጭር ጊዜ ለኢንተርፕራይዞች አገልግሎት እንዲሰጡ መደረግ አለበትም ነው ያሉት።

Exit mobile version