አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በዚህም ህገወጥ ይዞታን በተመለከተ፣ የቦታ ደረጃ የሊዝ ማሻሻያ መነሻ ዋጋ ክለሳን በተመለከተ እና በተለያዩ አልሚዎች የተወሰዱ መሬቶችን የተመለከቱ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
1ኛ:- ህገወጥ ይዞታን አስመልክቶ የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት ይዘት የተመለከተ ሲሆን÷ ጥናቱ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦችን እንዲሁም አማራጮችን ያመላከተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በጥናቱ ላይም ውይይት ከተደረገ በኋላ የተገኙ ሃሳቦችንና ግብአቶችን አካቶ ለድጋሚ እይታ እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፏል።
2ኛ:- የቦታ ደረጃ የሊዝ ማሻሻያ መነሻ ዋጋ ክለሳ ጥናት ተደርጎ በቀረቡት አማራጮች የሊዝ መነሻ አዋጅ ላይ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
3ኛ:- በተለያዩ አልሚዎች የተወሰዱ መሬቶች አስመልክቶ ውሳኔ ማስተላለፉን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC(Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!