Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ከተማ ከ350 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ በ352 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ባሮ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ተመርቆ ስራ ጀመረ።

በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት፤ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነውን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ በክልሉ ፋብሪካዎችን መገንባት የማይተካ ሚና አለው።

ፋብሪካው ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ጠቅሰው፤ መሰል ተግባራት ተጠናክርው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ለፋብሪካው የገበያ ትስስር እንዲኖርና የተለያዩ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

የፋብሪካው ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀይማኖት ደሳለኝ በበኩላቸው ፋብሪካው ብስኩት አምራች እንደሆነ ተናግረው፤ በቋሚነት 280 እንዲሁም በጊዜያዊነት ለ50 ሰዎች የስራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል።

ለግብዓት እጥረት ምላሽ ለመስጠት የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንዳይለያቸውም ጠይቀዋል።

Exit mobile version