Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል አማራጮች የ2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ብር ግብይት ተፈጽሟል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በዲጂታል አማራጮች የ2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ብር ግብይት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

የባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ዲቪዥን የመርቸንትና የኤጀንት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ብሌን ኃይለሚካኤል÷ በስድስት ወራት የዲጅታል ግብይት እንቅስቃሴውን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

አሁን ላይ ከ12 ሚሊየን በላይ የኤ.ቲ.ኤም ካርድ ተጠቃሚዎች፣ ከ9 ሚሊየን በላይ የሞባይል ባንኪንግና ከ20 ሚሊየን በላይ ሲቢኢ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል አማራጮችን የሚጠቀሙ የባንኩ ደንበኞች ቁጥር በየዓመቱ ከፍተኛ እድገት እያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በተያዘው በጀት አመት ስድስት ወራት ከ494 ሚሊየን በላይ ግብይቶች በዲጂታል አማራጮች ተከናውነው የ2 ነጥብ 8 ትሪሊየን ብር ግብይት መፈፀሙንም ነው የተናገሩት።

ግብይቱ ከአምናው ተመሳሳይ ውቅት ጋር ሲነፃፀር የ35 በመቶ እንዲሁም በገንዘብ መጠን የ118 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ አዳዲስ የዲጅታል አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ ለማቅረበ መዘጋጀቱንም ዳይሬክተሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የዲጂታል ባንኪንግ ደንበኞች ጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ሳይኖር በእጅ ስልክና በካርድ አማካኝነት አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓት መሆኑ ይታወቃል።

 

Exit mobile version