Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ትናንት የተከፈተው የዲፕሎማሲ ዐውደ-ርዕይ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት በሣይንስ ሙዚዬም “ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል መሪ ሐሳብ የተከፈተው የዲፕሎማሲ ዐውደ-ርዕይ ዛሬ በፓናል ውይይት ቀጥሏል።
በውይይቱ ላይም÷ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አንጋፋ ዲፕሎማቶች፣ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ሚሲዮኖች እንዲሁም የታሪክ ምሁራን እየተሳተፉ ነው።
በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ጉዞ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች በአንጋፋ አምባሳደሮችና ምሁራን እየቀረቡ ነው፡፡
የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፤ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ስኬት እና ድል በትውልድድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰ ነው ብለዋል።
በፓናል ውይይቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ኤምሬተስ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ፣ አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ፣ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና ዶ/ር አብደታ ዲሪባ የመነሻ ጽሑፍ እያቀረቡ ሲሆን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ታየ አጽቀሥላሴ ደግሞ መድረኩን በአወያይነት እየመሩት ነው።

በተያያዘም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሶስት ዓመታት የዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴን የያዘና የመጀመሪያው የሆነውን ዓመታዊ መጽሐፍ አስመርቋል።

በፍሬሕይወት ሰፊው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version