Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በሙስና መከላከል ሥራ ከ876 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በሙስና መከላከል ሥራ ከ876 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን የከተማዋ የሥነ-ምግባርና የጸረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አሰፋ ቶላ እንዳሉት÷ ባለፉት ስድስት ወራት ሙስናን ለመከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ሌሎች ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ሙስና በስፋት የሚስተዋልባቸው ዘርፎችን በመለየት የመከላከል ሥራ ላይ በትኩረት መሰራቱን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም በመደበኛ መከላከል 534 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና በአስቸኳይ መከላከል 342 ነጥብ 4 ሚሊየን በድምሩ 876 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት ማዳን መቻሉን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም በአይነት 171 ጠቅላላ ንብረት እና ከ4 ሺህ 685 ካሬ ሜትር በላይ መሬት ማዳን መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ከወንጀሉ ጋር በተያያዘም 136 ሰዎች ተጠያቂ መደረጋቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ 792 ጥቆማ መቅረቡን ጠቁመው ÷ ከእነዚህ ውስጥ የተጠና 592 እና አግባብነት የሌላቸው 21 ሲሆን÷ ቀሪዎቹ ደግሞ በሒደት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡

Exit mobile version