Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሠራዊቱ ተልዕኮውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲፈጽም አቅም የመገንባቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ሌ/ጄ ዘውዱ በላይ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከህዝብ የወጣና ለህዝብ የሚቆም ሠራዊትተልዕኮው ያለ ጦርነት የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር ነው ሲሉ የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ገለጹ።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ እንዳሉት ፥ ሠራዊቱ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚመጣ ጠላትን በመመከት የህዝቡን ሰላም እያስከበረ ነው።

ከህዝብ የወጣና ለህዝብ የሚቆም ሰራዊት ተልዕኮው ያለ ጦርነት የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር ነው ያሉት ዋና አዛዡ ፥ ጦርነቱን በድል በማጠናቀቅ ህዝቡን ወደ ቀደመ ሠላሙ የመመለስ ተልዕኮ ያለው እንደሆነ ተናግረዋል።

በመሆኑም ሠራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ መፈፀም የሚያስችለውን አቅም በመገንባት ረገድ የተሄደው ርቀትም የሚደነቅ መሆኑን ነው የገለጹት።

ሠራዊቱ ተልዕኮውን በአስተማማኝ ሁኔታ መፈፀም የሚያስችለውን አቅም የመገንባቱ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ሁሉ በድል እየተወጣ ያለ ሰራዊት ነው” ያሉት ደግሞ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተንኩዌይ ጆክ ናቸው።

ሠራዊቱ ሀገሪቱ በየጊዜው የሚገጥሟትን የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በመመከት ለሉዓላዊነቷ መከበር ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ያለ የህዝብ ልጅ መሆኑን እያስመሠከረ ያለ ሰራዊት እንደሆነ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version