አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ገዢ ኢትዮጵያዊ ትርክት የተንፀባረቀበት እንደነበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት የምስጋናና ዕውቅና አሰጣጥ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ፥ በዓሉ የብዝሃነት፣ የእኩልነትና የአንድነት እሳቤዎችን ባነገበ መልኩ ተከብሮ ማለፉን አስታውሰዋል።
ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ከፍ ባደረገ መልኩ ገዢ ኢትዮጵያዊ ትርክት የተንፀባረቀበት እንደነበር ጠቁመው ፥ ይህም ኢትዮጵያ አንዱ የበታች ሌላው የበላይ ሆኖ የሚኖርባት ሀገር እንዳልሆነች ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ መዋቅር ጀምሮ የተለያዩ አካላት ላደረጉት አስተዋፅኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በዓሉን ለማስተናገድ ሃላፊነት በመውሰድ በደመቀ ሁኔታ እንዲከበር የሶማሌ ክልል ያከናወነው ሥራ አድናቆት የሚቸረው እንደሆነም ነው የገለጹት።
በምስጋና እና ዕውቅና መርሐ ግብሩ አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ምክትል አፈ ጉባኤ ዘሀራ ዑመድ ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በወንድሙ አዱኛ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!