Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በባሕር በር አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ መድረክ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2016 ( ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በባሕር በር አስፈላጊነት እና ጥቅሞቹ ዙሪያ በተለይም ከኢትዮጵያ አንፃር እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
“የባሕር በር እና ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎቹ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይት ላይ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው፡፡
ውይይቱ ኢትዮጵያ እያቀረበች ያለውን የባሕር በር ተጠቃሚነት በተመለከተ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በመድረኩም “የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀይ ባሕር ጂኦ ፖለቲካ” እንዲሁም “የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር” የሚሉ ጥናታዊ ጽሑፎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
በለይኩን ዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
See insights and ads
Boost post
Like

 

Comment
Share
Exit mobile version