Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በድሬዳዋ ለሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር ለሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተካሂዷል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ለእንግዶች የተለያዩ መርሐ ግብሮችን ያዘጋጀ ሲሆን÷ በዛሬው እለትም የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንድስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት የእራት ግብዣ ተከናውኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፈቲያ አደን፣ የካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ ከፍተኛና እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በሌላ በኩል ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን በከተማዋ ያሉ የልማት ስራዎችን መጎብኘታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ያስተላለፉትን ጥሪ ተከትሎ ወደ ድሬዳዋ ዳየሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን መግባታቸው ተነግሯል፡፡

Exit mobile version