Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ሽመልስ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ በመሸለማቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ መሸለማቸውን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው÷“ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በድጋሚ ላገኙት ዓለም አቀፍ እውቅና መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተበረከተላቸው ይህ ገናና ሽልማት በአንድ በኩል ፖሊሲዎቻችንና ስትራቴጂዎቻችን አሸናፊ መሆናቸውን ለሁሉም አካል ያረጋገጠበትና የተያያዝነውን የብልፅግና ጉዞ አጠንክረን እንድንቀጥል የሚያነሳሳን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ይህ ቀጣይ ስኬት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ድልና ክብር ማሳያ መሆኑንም አቶ ሽመልስ አመላክተዋል፡፡

Exit mobile version