አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆናቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከየካቲት 6 እስከ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው ፈተና ከ112 ሺህ በላይ ነባርና አዳዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ማድረጋቸውን በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰዒድ መሃመድ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
የፈተና ጥያቄዎች ፣ የኮምፒውተር ፣ ፈተና የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች ልየታን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ነው ኃላፊው የገለፁት።
ፈተናው መቀሌ አክሱም እና አዲግራት ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥም ነው የገለጹት ።
አክለውም ፥ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ቢያጋጥም ችግር እንዳይፈጠር በሁሉም የፈተና ማስጫ ማዕከላት ጄነሬተር ዝግጁ መደረጉንም አብራርተዋል።
ባለፈው ዓመት በፈተና አሰጣጥ ሂደትያጋጠሙ ችግሮች ዘንድሮ እንዳይደገሙ በቂ ዝግጅት መደረጉን አቶ ሰኢድ ተናግረዋል፡፡
በመሳፍንት እያዩ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!