አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የስራ ሀላፊዎች በሀላባ ዞን የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ጉበኙ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተመራው ልኡክ በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በየዬ ቀበሌ የበቆሎ ሰብሎችን እና ሌሎች የበልግ አዝመራዎችን ጎብኝተዋል።
የቀበሌው አርሶ አደሮች ለምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ በአሁኑ ሰዓት የደረሰውን የበቆሎ እሸት ወደ ገበያ ለማድረስ የቫይረሱ ወረርሽኝ ችግር እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል፡፡
የገጠማቸውን የገበያ ችግር እንዲፈታላቸውም መጠያቃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳ ከአርሶ አደሮቹ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ እንዳሉት የደረሱ ሰብሎችን ወደ ገበያ ለማቅረብ የገጠመውን ችግር ለመፍታት በክልሉ ህብረት ስራ ማህበራት በኩል የገበያ ትስስር ይደረጋል ብለዋል ፡፡

