Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመጀመሪያው የአፍሪካ ቡና ሳምንት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉበት የመጀመሪያው የአፍሪካ ቡና ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ ( ዶ/ር)፣ የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ለአንድ ሳምንት በሚቆየው መርሐ-ግብርም÷ የ25 ቡና ላኪ አፍሪካ ሀገራትና የቡና ገዢ ሀገራት የግብርና ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቡና ሳምንት ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መርሐ-ግብሩ የአፍሪካ የቡና አምራችና በዘርፋ የተሰማሩ አካላት የልምድ እና የእውቀት ልውውጥ የሚያደርጉበት መድረክ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለቡና ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት ያላትና ያልተነካ አቅም ባለቤት መሆኗን ገልጸዋል፡፡

መንግስትም ለዘርፋ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

እንዲሁም 20ኛው የአፍሪካ ፋይን ኮፊ አሶሴሽን ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ከጥር 29 እስከ የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ተጠቅሷል፡፡

በበረከት ተካልኝ

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version