Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ ንቁ ተሳትፎ እንደምታደርግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ ለልማት አጋርነት እና ትብብርን ማጎልበት፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና የባለብዙ ወገን ሥርዓት መጠናከርን በመደገፍ ቀዳሚ ትኩረት በመስጠት ንቁ ተሳትፎ እንደምታደርግ ተገለጿል፡፡
 
ሁለተኛው የኢትዮጵያ የብሪክስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኮሚቴ ስብሰባ በትናንትናው ዕለት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዳራሽ ተካሂዷል።
 
ከተለያዩ የፌደራል ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያን ከብሪክስ እንቅስቃሴ ጋር በማዋሃድ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር አድርገዋል።
 
በብሪክስ ማዕቀፍ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ መንገድ ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል።
 
ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ ለልማት አጋርነት እና ትብብርን ማጎልበት፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና የባለብዙ ወገን ሥርዓት መጠናከርን በመደገፍ ቀዳሚ ትኩረት በመስጠት ንቁ ተሳትፎ እንደምታደርግ መመላከቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version