Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ8 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ ደርሷል -ኮርፖሬሽኑ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጪ ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን ከ8 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሚሆነው ጅቡቲ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ገልጿል፡፡

ትናንት 510 ሺህ ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ወደብ በመድረሷ እስካሁን ከውጪ ወደ ወደብ የተጓጓዘው የማዳበሪያ መጠን ወደ 8 ሚሊየን 146 ሺህ 606 ኩንታል ከፍ ማለቱ ተጠቁሟል፡፡

ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ እስካሁን 6 ሚሊየን 901 ሺህ 212 ኩንታል ወይም 85 በመቶ የሚሆነው ወደ ሀገር ውስጥ ተጓጉዞ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ከሰባት ቀናት በኋላ 738 ሺህ ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ የጫነች መርከብ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version