አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና በዛሬው ዕለት በጤና መርሐ-ግብሮች መሰጠት መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ዛሬ መሰጠት በጀመረው የመውጫ ፈተናም ጠዋት 15 ሺህ 440 ተማሪዎች በ23 የጤና መርሐ-ግብሮች መፈተና መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ከሰዓት 14 ሺህ 807 ተማሪዎች በ13 መርሐ-ግብሮች ፈተና መውሰዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
የሁለተኛው ዙር ፈተና በ47 የመንግሥት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት እንደሚሰጥም ተመላክቷል፡፡
በመንግሥትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149 ሺህ 145 ተፈታኞች በ204 የፈተና መርሐ-ግብሮች ፈተና እንደሚወስዱ ተጠቁሟል፡፡
ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተናም የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!