አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጃፓን ዓለም ዓቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ተልዕኮዎች እንዲሳኩ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የጃይካ የኢትዮጵያ ጽ/ቤት ዋና ተጠሪ ከንሱኬ ኦሺማ ከብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም አምባሳደር ተሾመ÷ የጃፓን መንግስት የቀድሞ ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም ለሚደረገው ጥረት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በተለይም ጃይካ ለቀድሞ ተዋጊዎች ምዝገባና ዲጅታል መታወቂያ ዝግጅት የሚያገለግሉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችና የሙያ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት ማሳየቱን አድንቀዋል፡፡
በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት መካከል ሊኖሩ ስለሚገቡ የትብብርና አጋርነት መስኮች እና የአፈፃፀም አግባቦችን በመለየት ከመግባባት ላይ መደረሱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡