አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ እና በሚዛን አማን ከተሞች ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
መድረኩ “ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
በቦንጋ ከተማ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በተመሳሳይ በሚዛን አማን ከተማ ሕዝባዊ የውይይት መድረክ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ጌታሁን አብዲሳ እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በውይይት መድረኮቹ ከሕብረተሰቡ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ቀረበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በአብዱ ሙሃመድ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!