Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለህዝብ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በመስጠት የተሻለ ነገ ለመፍጠር በቁርጠኝነት ይሰራል – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢ ምላሽ በመስጠት የተሻለ ነገ ለመፍጠር የተዘጋጀ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ተናገሩ።

በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ላይ ተሳታፊዎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎችን እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን በኩል መንግስት ይበልጥ ትኩረት በማድረግ የህዝብን ጥያቄ መልስ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።

በድሬዳዋ ከተማ የሚስተዋለው ሰላማዊ ሁኔታ ለሌሎቹ አካባቢዎችም ምሳሌ የሚሆን ነው ያሉት ተወያዮቹ÷ ይሄም አመራሩ ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ የመስራቱ ውጤት ነው ብለዋል።

በመሆኑም ሌሎች አካባቢዎች የድሬዳዋን መልካም ተሞክሮ ሊተገብሩ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ ለተነሱ ሃሳቦችና ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፣ የከተማዋ ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የአስተዳድሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው፡፡

በዚህም በውይይቱ ላይ የተነሱ ጥያቄዎችን በከተማ አስተዳድሩ እና በፌደራል ደረጃ መፍትሄ ለመስጠት በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

በይስማው አደራው

 

Exit mobile version