አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኬንያ አቻቸው ኪሮሪ ሲንግኦኢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሁለትዮሽ ትብብሩን ማስፋፋትና የበለጠ ማሳደግ እንደሚገባ ከመግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡
የኢኮኖሚ ትብብሩን የበለጠ ለማጠናከርም የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን በቅርቡ እንዲካሄድ መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የላፕሴት ፕሮጀክት ለቀጣናዊ ውህደት ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው እና ከሁለቱም ሀገራት ባሻገር ለቀጣናውም ፋይዳ እንዳለው በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡