አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤኒን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ገለጸች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቤኒን አቻቸው ኦሉሸጉን ባካሪ ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፥ ቤኒን በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን የማይናወጥ ቁርጠኝነት ማድነቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኦሉሼጉን ባካሪ በበኩላቸው ፥ ቤኒን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም ትፈልጋለች ብለዋል።
ሚኒስትሮቹ የፖለቲካ ግንኙነቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማሳደግ ትክክለኛው ጊዜ አሁን እንደሆነም ነው የተስማሙት፡፡

