አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በነዳጅ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እና በኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት መካከል በነዳጅ ልኬት መሳሪያ ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት በርካታ ተሽከርካሪዎች ከ5 ቀናት በላይ በሱሉልታ ቆመዋል።
አሽከርካሪዎቹ ከጅቡቲ ጭነው ያመጡትን ነዳጅ ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት በነበረው ዲፒስቲክ የተባለ መሳሪያ ለክቶ ይቀበለን ይላሉ።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በበኩሉ ይህ አሰራር ኋላቀር ስለሆነ ባልክሜትር በተሰኘ መሳሪያ ነው ለክቼ የምቀበላችሁ የሚል ምላሽን ይሰጣል።
የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ሀይለማርያም፥ አሽከርካሪዎቹ የጫኑት ነዳጅ በዲፒስቲክ መሳሪያ እንዲለካ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
በዲፒስቲክ መሳሪያ ልኬት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን የሚሞላው ባልክ ሜትር የተሰኘ መሳሪያ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑንም ነው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት።
ስራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ አክለውም፥ የነዳጅ ማደያዎች ጭምር ባልክሜትር የተሰኘውን የልኬት መሳሪያ እንዲጠቀሙ ጠይቀዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

