አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር ኢ/ር) ከአሜሪካ ኮንግረስ አባል ጆናታን ጃክሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል ባለው ዘርፈ ብዙ ግንኙነት አስፈላጊነት ዙሪያ መክረዋል፡፡
በዚህም በአጎዋ፣ ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት በምታደርገው ጥረት እና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች በቀጣይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ለመለዋወጥና በትብብር ለመስራት መስማማታቸውንም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡