አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የመኪና ማቆሚያ ችግር ለመፍታት እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ገልጿል።
በዚህም ነባር የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በማሻሻል ወደ አገልግሎት የማስገባት ስራ እየተሰራ እንደሆነና የህንፃ ባለቤቶችም ለመኪና ማቆሚያ በሚል ያዘጋጁትን ቦታ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲያውሉ የሚደነግግ ህግ በቅርቡ ይወጣል ብሏል።
ተሽከርካሪዎች ከእንቅስቃሴ ይልቅ በመቆም ብዙ ጊዜ እንደሚያሳልፉ የባለስልጣኑ የፓርኪንግ ጥናት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጌታቸው አንስተዋል፡፡
በመዲናዋ የተሽከርካሪዎች ቁጥር እየጨመረ የመምጣቱን ያህል የመኪና ማቆሚያ አቅርቦት ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ ለችግር መፍትሄ ለመስጠት በማለም በተለያዩ ቦታዎች ላይ አዳዲስ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን እያዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከሚዘጋጁት የመኪና ማቆሚያዎች ባሻገር በከተማዋ በሚገኙ ህንጻዎች ስር ያሉ ማቆሚያዎችን በአስገዳጅነት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ በማድረግ ለችግሩ አማራጭ መፍትሄ መቀመጡን ጠቁመዋል።
በመዲናዋ የተገነቡት የግለስብ እና የመንግስት ህንፃዎች ባላቸው የመኪና ማቆሚያ ቦታ ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነም አቶ ቢንያም ገልጸዋል፡፡
ቦታዎቹን ለታለመላቸው ዓላማ ለማዋል የሚያስችል አስገዳጅ የሆነ የሕግ ረቂቅ ተዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል መቅረቡን እና በዚህ ዓመት ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በሲሳይ ጌትነት
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!