Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የገርዓልታ ሎጂ ግንባታ በ1 ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል- አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አካል የሆነው ገርዓልታ ሎጅ በአንድ ዓመት ውስጥ ተጠናቅቆ ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሑሴን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የፌደራልና የክልል አመራሮች የገርዓልታ ሎጅ የሥራ ሁኔታን ጎብኝተዋል፡፡

ከጉብኝቱ በኋላም ውይይት ማድረጋቸውን አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ከአካባቢው ጋር የተጣጣመ ኢኮ-ሎጅ መሆኑን ጠቅሰው÷ ተፈጥሮ ባደለው የተራራ ሰንሰለቶች ላይ መገንባቱን አመላክተዋል፡፡

ሥራው ሲጠናቀቅም ከተመራጭ የጎብኚ መዳረሻ ሥፍራዎች አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል::

ፕሮጀክቱ እንደቀደሙት ሌሎች ፕሮጀክቶች ጥብቅ አፈፃፀም፣ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግበት ገልጸው÷ በአንድ ዓመት ውስጥም ተጠናቅቆ ለሕዝብ ክፍት ይሆናል ተብሎ እንደታመነበት አንስተዋል፡፡

Exit mobile version