Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጎንደርና የአምቦ ከተማ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር እና የአምቦ ከተማ ከንቲባዎች በአዲስ አበባ ከተማ በመገንባት ላይ ያሉ የልማት ስራዎችን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።

የጎንደር ከተማ ከንቲባ ኢንጂነር ማስተዋል ስዩም እና የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰሃሉ ድሪብሳ እንዲሁም ከሁለቱም ከተማዎች የተወጣጡ የሀገር ሽማሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር በመሆን ነው በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን የጎበኙት።

የሁለቱ ከተማ ከንቲባዎችና ልኡካኑ የእንጦጦ ፓርክ፣ ሸገርን የማስዋብ፣ የአድዋ ማዕከል እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የከንቲባ ጽህፈት ቤት ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በከተማዋ በግንባታ ላይ ያሉ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል እና ተፈጥሯዊ መስህቦች በእጅጉ የሚያጎሉና ለሌሎች ከተማዎች ምሳሌ እንደሚሆኑ ከንቲባዎቹ ተናግረዋል።

ከጉብኝቱ በኃላ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሁለቱ ከተማዎች ከንቲባዎች እና የህዝብ ተወካዮች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ዙሪያ በጋራ መክረዋል።

በዚሁ ወቅት ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ አዲስ አበባ የሀገሪቱና የአፍሪካ መዲና እንደመሆነኗ ከሌሎች የሀገራችን ከተማዎች ጋር በጋራ ለመስራትና ልምድ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version