Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በመጀመሪያ ቀን ውሎው የጠዋት መርሐ ግብሩ የጉባኤው አጀንዳዎች ቀርበው አባላት ከተወያዩ በኋላ እንደሚያጸድቁ ይጠበቃል።

በመቀጠልም የክልሉ መንግሥት የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወር የልማት እና የመልካም አሥተዳደር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረጋል።

ምክር ቤቱ በሦስት ቀን የጉባኤ ቆይታው የተለያዩ ሪፖርቶችን አድምጦ እንደሚያጸድቅ አሚኮ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር እና የተለያዩ ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ተገልጿል፡፡

Exit mobile version