Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሔራዊ የሽግግር ፍትሕ ረቂቅ ፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።
 
የሽግግር ፖሊሲ የባለሙያዎች ቡድን ላለፉት 8 ወራት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለፍትሕ ሚኒስቴር ማስረከቡ ይታወሳል።
 
በረቂቅ ፖሊሲውም በወንጀል ተጠያቂነት፣ የጊዜ ገደብ እና የሽግግር ፖሊሲውን ለመተግበር የሚያስፈልጉ አዳዲስ ተቋማት ተመላክተውበታል።
 
ሰብዓዊ መብት ተኮር ተግባር፣ ማንንም አለመጉዳት አውድ ተኮር አተገባበር እና ተጠያቂነት ረቂቅ ፖሊሲው የሚመራባቸው መርሆች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
 
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክሮች ከተደረጉ በኋላም ፖሊሲው ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
 
ዘላቂ ሰላም፣ እርቅ፣ የሕግ የበላይነት ፣ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ የሚረጋገጥበት መደላድል መፍጠር የረቂቅ ፖሊሲው ዓላማዎች መሆናቸውም ተብራርቷል፡፡
በበረከት ተካልኝ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version