Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አምባሳደር ፀጋአብ ኢትዮጵያ ከኦስትሪያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንግስት ከኦስትሪያ ጋር የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነትን የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን አምባሳደር ፀጋአብ ክበበው ገለጹ፡፡

አምባሳደር ፀጋአብ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኦስትሪያ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ቫን ደር ቤለን አቅርበዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ውይይትም በፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሂደትና ሌሎች አህጉራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለፕሬዚዳንቱ ገለፃ አድርገዋል።

አምባሳደሩ አያይዘውም የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እያደገ መምጣቱን በመጥቀስ የኢትዮጵያ መንግስት ከኦስትሪያ ጋር የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነትን ይበልጥ ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

መቀመጫቸውን በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ያደረጉት አምባሳደር ፀጋብ ክበበው ቪየና ለሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በኦስትሪያ በሚገኙ ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢፌዲሪ ቋሚ ተወካይ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version