አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ፖሊስ ኮሚሽን የዲሲፕሊን ግድፈት በተገኘባቸው 81 የፖሊስ አመራሮችና አባላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።
የህግ የበላይነት ሳይሸራረፍ ፍትህ ለማስፈን እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል ኮሚሽኑ ለ15 ቀናት የአመራርና የአባላት ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ነስሪ ዘከሪያ እንደገለፁት፤ በመድረኩ በፖሊስ አመራርና አባላት ላይ በሚታዩ የስነ-ምግባርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች ምክንያት ሁሉም አመራርና አባላት በግምገማው እንዲያልፉ ተደርጓል።
በዚህ ሂደትም በመንግስትና በህዝብ የተሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት ተጠቅመው ህብረተሰቡን ከማገልገል ይልቅ ለግል ጥቅማቸው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አመራሮችና አባላት ላይ በጥፋታቸው ልክ የዲሲፕሊን እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም የስራ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮች ከቦታቸው እንዲነሱ መደረጉን ጠቅሰው፤ በተደረገው ግምገማ 51 የፖሊስ አባላት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተናግረዋል፡፡
ከነዚህ ውስጥ 17ቱ በህግ እንዲጠየቁ፣ 15 አባላት 1 ወር ከስራና ደመወዝ እንዲታገዱ፣ 8 አባላት ለ2 ወር ከስራና ደመወዝ እንዲታገዱ፣ 7 የፖሊስ አባላት ደግሞ ለ1 እና 2 ወር ከስራና ደመወዝ ታግደው ከማዕረግ ዝቅ በማድረግ ከሀላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን ኮሚሽነሩ ጨምረው ገልፀዋል።
በግምገማው ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ በዘርፉ የተጀመረውን የሪፎርም ስራ ከማሳካት ባሻገር በአገልግሎት አሰጣጥ የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ እንደሚሰራ መጠቆማቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!