Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ጉባዔው ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷ በቆይታውም የክልሉ መንግሥት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚገመገም ተገልጿል፡፡

የምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ረቂቅ ደንብን ጨምሮ ልዩ ልዩ አዋጆች እና የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባዔ ቃለ ጉባዔ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል፡፡

Exit mobile version