Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ተሽከርካሪዎችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ተሽከርካሪዎችን የሰረቁ ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር አውሎ ተሽከርካሪዎቹን ማስመለሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ ሲያስማሙ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ነው የተገለፀው፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8  ልዩ ቦታው ገነት ወይም ጨፌ ኮንደሚንዬም ግቢ ውስጥ  ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ነው።

ንብረትነታቸው የግል ተበዳዮች የወ/ሮ ቤተልሔም ሃይሉ እና የአቶ ያሬድ መቻል የሆኑ  አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ  ተሽከርካሪዎች ለማሳደር ካቆሙበት ቦታ መሰረቁን  በተመለከ ለፖሊስ ሪፖርት መድረሱ ተገልጿል፡፡

ፖሊስ የግለሰቦቹ አቤቱታ መነሻ በማድረግ ባደረገው ክትትል አራት ወንጀል ፈፃሚዎች  ሁለቱንም ተሽከርካሪዎች በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አለም ባንክ እና በሸገር ከተማ ፉሪ አካባቢ ደብቀው ለመሸጥ በማስማማት ላይ እንዳሉ  እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው ከግል ተበዳዮች ጥበቃ ሰራተኞች ጋር በመመሳጠርመሆኑን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ ላይ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ክስ ለመመስረት ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓድዋ ዘመን የታየው የሀገርና የወገን ፍቅር ዛሬም ፀንቶ እንዲቀጥል መሥራት ይጠበቃል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ለሀገር የሚከፈል ዋጋ ከምንም በላይ ነው ብለዋል፡፡

ዓድዋ ሀገር የሚታደግና የሚያጸና ትምህርት ቤት በመሆኑ ስብራቶችን ለመጠገን ፍቱን መድሃኒት እንደሆነም አመላክተዋል።

Exit mobile version