አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዓድዋ ድል የወረስነውን መልካም ዕሴት በመከተል ለመጪው ትውልድ ኩራትና ክብር የሚሆን ዐሻራ ለማኖር ሁላችንም መረባረብ ይጠበቅብናል ሲሉ ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ 128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም÷ የሀገራችን ሕዝቦች በአንድነት ተሰባስበው ያሳኩት በመሆኑ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ብሔራዊ ገድልና ብሔራዊ ኩራት ነው ብለዋል፡፡
128ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ስናከብርም ጀግኖች አባቶቻችንን ያቆዩልንን የሀገራችንን ኅብረብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር ከነጠላ ትርክት ይልቅ ዓድዋን ለመሰሉ አሰባሳቢ ትርክቶች ትኩረት በመስጠት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡
ከለውጡ በኋላ የመጣው መንግሥትም ለዚህ ታላቅ ድል ትኩረት ሰጥቶ የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመገንባት አሰባሳቢ ትርክት ለመፍጠር በመሥራቱ መመስገን እንዳለበት ጠቅሰዋል፡፡
ከዓድዋ ድል የወረስነውን በሀገር ጉዳይ ልዩነትን ወደ ጎን ትቶ የመተባበርና ለአንድ ዓላማ በአንድነት የመሰለፍ መልካም ዕሴት በመከተል የእርስ በርስ ግጭትና አለመግባባትን አስወግደን ለመጪው ትውልድ ኩራትና ክብር የሚሆን ደማቅ ዐሻራ ለማኖር ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!