Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመጀመሪያው የትምህርት ምዘና ብሔራዊ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የትምህርት ምዘና ብሔራዊ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባዔው “በኢትዮጵያ የትምህርት ምዘናና የፈተና አሰጣጥ ስርዓቶችን መለወጥ፤ የነገ ትልሞችን ለማሳካት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በጉባዔው የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር)፣ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የተማሪዎችን ውጤታማነት ለማሳደግ የትምህርት ምዘና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች፣ ሀገር አቀፍ ፈተናዎችና የትምህርት ምዘና ላይ ለውጥ ለማምጣት አዳዲስ ሀሳቦችና ተሞክሮዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ጉባዔው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተጠቁሟል።

Exit mobile version