Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አብርሃም በላይ (ዶ/ር) ከኳታር የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ካሊድ ቢን መሐመድ አል አቲያህ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም÷ የጋራ ጉዳዮችን እንዲሁም የሁለቱን ወገኖች የትብብር ግንኙነት ማጠናከርና ማጎልበት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ዘ ፔኑሱላ ኳታር ዘግቧል።
 
በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የኳታር ወታደራዊ አታሼ ብርጋዴር-ጄኔራል መሐመድ አሊ አል ሀጅሪ እንዲሁም በርካታ የሁለቱም ወገኖች ከፍተኛ ባለስልጣናት እና መኮንኖች ተገኝተዋል።
 
ውይይቱ ከ8ኛው የዶሃ ዓለም አቀፍ የባህር መከላከያ አውደ ርዕይ እና ኮንፈረንስ ቀደም ብሎ መካሄዱ ተመላክቷል፡፡
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version