አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በከርሰ ምድር እንፋሎት (ጂኦተርማል) ኃይል ላይ አብሮ ለመስራት መስማማታቸው ተሰምቷል፡፡
በሩሲያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ቻም ኡጋላ ኡሪያት ኢትዮጵያና ሩሲያ በጂኦተርማል ሃይል ዘርፍ ላይ ስምምነት ለመፈራረም እንደታሰበ ገልጸዋል፡፡
አምባሳደሩ ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፥ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በስምምነቱ ላይ እየተወያዩ ነው ብለዋል።
ሩሲያ በዘርፉ የላቀ እውቀት ባለቤት ያሉባት እንደሆነች እንገነዘባለን ያሉት አምባሳደር ቻም ኡጋላ፥ ኢትዮጵያ የኃይል አቅርቦቷን ማሳደግ እንደምትሻም ተናግረዋል፡፡
በዚህም ሀገራቱ ስምምነት ለማድረግ መቃረባቸውን ገልጸው፥ የሩሲያ ኩባንያ ሩስጊድሮ ሊሰራበት የሚፈልገው ፕሮጀክት እንዳለም ነው የጠቆሙት፡፡
#Ethiopia #Russia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!