Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልጽግና ፓርቲ ልዑክ በጅቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው ልዑክ በጅቡቲ የገዢው ፓርቲ 45ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
 
በመርሃ-ግብሩ አቶ አደም ፋራህ የአጋርነት ንግግር ያቀረቡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ለገዢው ፓርቲ እና ለጅቡቲ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
አክለውም ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ የባህል እና የቋንቋ ትስስር ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ከመሆናቸው ባሻገር በኢኮኖሚያዊ እና በመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ዝርጋታ የጠበቀ ግንኙነት እንዳለቸው አንስተዋል።
በመጨረሻም የብልጽግና ፓርቲ ለጅቡቲ ገዢው ፓርቲ ያለው አብሮነት እና ወንድማማችነት ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኛ አቋም በመግለጽ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
 
በክብረ-በዓሉ ላይ የቻይና፣ የኬንያ እና ሩዋንዳ ልዑክ መገኘታቸውን ከጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version