Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዘንድሮ ክረምት 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም የክረምት ወቅት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩን ለማሳካት የቅድመ ዝግጅት ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑን በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ፋኖሴ መኮንን ገልጸዋል፡፡
 
ከ6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞች ውስጥም 60 ከመቶው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ ዛፍ ችግኞች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
የሚዘጋጁ ችግኞች የሚተከሉባቸውን ተፋሰሶችን የማልማት ስራ እየተሰራ እንደሆነም አመላክተዋል፡፡
 
ይህንን ለማሳካትም ከአፈርና ውሀ ጥበቃ ሥራው ጎን ለጎን ለችግኞቹ ተስማሚ የሆነ የተከላ ቦታ ዝግጅት አካባቢያዊ ካርታ የመለየት ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
 
የችግኝ ጣቢያዎችን ለማሳደግ በተሰራው ሥራ በ132 ሺህ 144 ችግኝ ጣቢያዎች ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩ የታቀዱት 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን የማፍላት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡
 
በመሆኑም የግብርና ባለሙያዎችና አርሶ አደሮች ዝግጅታቸውን በተገለጸው ልክ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡
 
በታምራት ቢሻው
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version