Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀገር አቀፍ የጤና አገልግሎት ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው ሀገር አቀፍ የጤና አገልግሎት ኢኖቬሽንና ጥራት ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል::
 
ጉባኤው “የጤና ስርዓት ኢኖቬሽንን በማጎልበት የጤና አገልግሎት ጥራት ደህንነትና ፍትሃዊነትን ማሻሻል” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው::
 
በጉባኤው ላይ የተለያዩ የፌደራልና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የሙያ ማህበራት፣ አጋር ድርጅቶች፣ የምርምር ተቋማት እንዲሁም የተለያዩ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው::
 
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት እንደሚካሄድ ተነግሯል::
 
በዘቢብ ተክላይ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version