አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ስካውት ብሔራዊ ጃምቡሬ ቀንን በማስመልከት ከኢትዮጵያ ስካውት መሪዎችና አባላት ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም ርዕሰ መስተዳድሩ የኢትዮጵያ ስካውት ብሔራዊ ጃምቡሬ ቀን ሲከበር የሀረርን የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶቿን ይበልጥ በማንፀባረቅና የከተማውን ገፅታ በመገንባት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ስካውት ብሔራዊ ጃምቡሬ ቀን አከባበር መርሃ ግብር ከኢትዮጵያ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ታዳጊ ወጣቶች የባህልና የልምድ ትውውቅና አብሮነትን የሚፈጥር ልምድ እንደሚያገኙበት ተናግረዋል።
የብሄር፣ የሀይማኖት፣ የአካባቢ አጥሮችን በማፍረስ ብሔራዊነትን በመገንባት በሀገር ፍቅር አርበኝነት የተገነባ ትውልድን ማፍራት የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን አመላክተዋል።
በዓለም ለ14ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ8ኛ ጊዜ የሚከበረው የስካውት ብሔራዊ ጃምቡሬ ቀን ከሀምሌ 15 ጀምሮ በሐረር ከተማ እንደሚከበር መገለፁን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡